ብቸኛው ቀላል የንግድ ተሽከርካሪ ጠንካራ ጭነት ተሸካሚ ቻንሲ እና ከፍተኛ አፈፃፀም እገዶች ያለው ሆኖ የተገነባ ፣ ቀላል ለተለያዩ ተልእኮዎች እንዲበጅ የተደረገ። ከ Daily 4x4 ቫን ወይም ካብ ከእንግዲህ ሊደረስበት የሚችል ቦታ የለም ፡፡ እጅግ በጣም አስቸጋሪ የሆኑ መሬቶች ወይም በተደበላለቀ አስቸጋሪ እና ታምቡር መንገዶች ላይ በቀላሉ ለመስራት ትክክለኛውን የመንገድ ላይ እና ከመንገድ ውጭ በሁለቱም ስርቶች የተዘጋጀ ኢቬኮ Daily 4x4 ቫን ወይም ካብን ይምረጡ።
እስከ 5000 ኪ.ግ. ድረስ የመጫን አቅም ያለው ቻንሲ ፍሬሙ ለየት ያለ ንድፍ ፣ አዲሱ የፊት አክስል ከግለልተኛ የፊት የክብደት እገታዎች ፣ ባለ 3-ቁራጭ የፊት መከለያ እና ሙሉው የዲስክ ብሬክስ በልዩ ሁኔታ የተሻሻለ የ ኢኤስፒ (ESP) ፕሮግራም Daily ን 4x4 በገበያው ላይ ብቸኛ ተሽከርካሪ ያደርገዋል። የደንበኞችን ፍላጎትን የሚያረካ ፣ ዘላቂ አፈፃፀም እና አስተማማኝነቱ የተመዘገበለት፡፡
ምስጋና ይግባውና Daily 4x4 ቫን ወይም ካብ ባለሁለት ዝቅተኛ ሬሾዎች ባለ 12 የፊት ማርሾች በማንዋል ትራንስሚሽን እና ባለ 16 አይ-ማቲቪ ትራንስሚሽን ጋር ይገኛል ፡፡ ያልተገደበ ከፍታ የመውጣት ችሎታ በከፍተኛ ሁኔታ ምቾትን የሚጠብቅ ፡፡ በዳሽቦርዱ ላይ የ ኢሮጎኖሚክ (ergonomic) በተን በማግበር የዝቅተኛ ፍጥነት ጥምርትን በቀላሉ ማስተካከል ይችላሉ።
Daily 4x4 ቫን ወይም ካብ በ ኤፍ1ሲ (F1C) ኢሮ 3 (Euro III 3.0) የሞተር ኃይል 150 የፈረስ ጉልበት እና 350 ኒውተን ሜትር እሽክርክሪት ሲሆን ሁሉንም ተልእኮዎች በቀላል ማከናወን ይችላል ፡፡
በትራንስሚሽን ሳጥን እና በ 4 ዓይነት ማያያዣዎች ላይ ኃይልን ከምንጩ የሚያስተላልፍ መሣሪያ (PTO) በመጠቀም ፣ Daily 4x4 ቫንዎን ወይም ካብዎን ለተለያዩ በርካታ ትግበራዎች መጠቀም ይችላሉ፡፡ Daily 4x4 ከመንገድ ውጭ ላሉት ለተለያዩ የመንገድ ላይ ትግበራዎች ሰፋ ያለ የተለያዩ ገፅታዎች ያቀርባል እና የማንሻ መሣሪያ ለመገጣጠም እንዲቻል ከፍብሪካው የተዘጋጀ ነው፡፡