IVECO S-WAY

አዲሱን ስሪት ያሽከርክሩ

ከቤትዎ ወደ ሌላኛው ቤትዎ

በአዲሱ ስሪት ጋቢናው፣ በከፍተኛ ነዳጅ ቆጣቢነቱ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂው IVECO S-WAY የጭነት መኪና ለአሽከርካሪዎች በማሽርከር ህይወታቸው ውስጥ ጥሩ ለረጅም ጊዜ የሚያሽከረክሩበት ሁኔታ ከመስጠት በተጨማሪ ለባለቤቶች ተወዳዳሪነታቸውን እና ጠቅላላ የባለቤትነት ወጪያቸውን በማሻሻል አሸናፊ የቴክኖሎጂ ውጤት ለማቅረብ ታስቦ የተዘጋጀ የተሟላ የትራንስፖርት የቴክኖሎጂ ውጤት ነው፡፡

የጭነት መኪናው የተዘጋጀው እያንዳንዱ አሽከርካሪ ለማሽርከር የሚያልመው የጭነት መኪና እንዲሆን ታስቦ ነው፡ ይህም ማለት የጭነት መኪናው የተዘጋጀው የአሽከርካሪዎችን ፍላጎቶች ታሳቢ ባደረገ መልኩ ሆኖ አዲሱ ጋቢናው ሰፊ ከመሆኑም በተጨማሪ የተለያዩ ምቾት ሰጪ ባህሪያትን እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ይዟል፡፡ የጭነት መኪናው በትክክልም ከቤትዎ ወደ ሌላኛው ቤትዎ የመሸጋገር ያክል ነው፡፡

IVECO S-WAY፡ አዲሱን ስሪት ያሽከርክሩ

2 IVECO S-WAYን የተመለከቱ ዝርዝር ማስረጃዎች

እስከ 4% ነዳጅ
ይቆጥባል
+
በአዲስ የጉዞ እንቅስቃሴ ጥናት እና የጋቢና ዲዛይን

የተሽከርካሪውን የጉዞ እንቅስቃሴ አፈጻጸም እጅግ ከፍ ለማድረግ ሲባል እያንዳንዱ ዝርዝር በጥንቃቄ ተጠንቷል፡ የአየር ፍሰትን ከፍ ለማድረግ እና በከፍተኛ ደረጃ የተሻሻለ የነዳጅ ስርጭት ውጤታማነት ለመፍጠር ሁሉም ቦታዎችና ክፍተቶች ተዘግተዋል፡፡

designed around the driver

የላቀ የማሽከርከር
ምቾት
+
የላቀ የማሽከርከር ምቾት

ሙሉው የሹፌሩ መቀመጫ አካባቢ የበለጠ ምቾትና እጅግ ጥሩ እይታ እንዲሰጥ ለማድረግ ሲባል ዲዛይኑ በድጋሚ ተዘጋጅቷል፡፡ አሽከርካሪው በጉዞ ላይ የሚብቃቸውን ሁኔታዎች ለማሟላት ሲባል እያንዳንዱ ዝርዝር በጥንቃቄ ተጠንቷል፡፡

premium driving comfort

ልዩ እና የተግባር ዲዛይን

አዲስ የጉዞ እንቅስቃሴ አፈጻጸም ደረጃና ስታይል
የማሽከርከር ስታይል/ዘይቤ
ሙሉ በሙሉ አዲስ ጋቢና
ዲዛይኑ ለተጠቃሚዎች ከነዳጅ ቁጠባና ዝቅተኛ የባለቤትነት ጠቅላላ ወጪ (TCO) አንስቶ እስከ ከፍተኛ የአሽከርካሪ ደህንነት ድረስ የተለያዩ ጥቅሞችን እንዲያስገኝ ከመሬት ከፍ እንዲል ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡
የተሽከርካሪውን የጉዞ እንቅስቃሴ አፈጻጸም በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ እያንዳንዱ ዝርዝር ተጠንቷል፡፡

ሙሉ በሙሉ አዲስ ፈረፋንጎ
በድጋሚ የተዘጋጀው የፈረፋንጎ ዲዛይን ከልዩ ተልዕኮዎችዎ መስፈርት ጋር የሚጣጣሙ የፕላስቲክ እና ቅይጥ የምርት ውጤቶች አማራጭ ይሰጥዎታል፡፡ የተለያዩ ክፍሎች ያሉት ፈረፋንጎ እርስዎንም ሆነ ተሽከርካሪዎን ከመከላከል በተጨማሪ – መቀየር የሚበቅብዎ የተጎዳውን ክፍል ብቻ በመሆኑ የጥገና ወጪዎችዎን ይቆጥብልዎታል፡፡

የጉዞ እንቅስቃሴ መሳሪያ
የጎማ ማራዘሚያዎቹ ለጥሩ የጉዞ እንቅስቃሴዎቹ እና ለንድፉ ውጤታማነት አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

ሙሉ የLED የፊት መብራቶች
​​አዲሱ ሙሉ የLED የፊት መብራቶች ዲዛይኑ ሁሉንም ለማየት የሚፈልጉትን እይታ እንዲያዩ ያስችልዎታል፡፡ በፊት መስታወቱ ላይ የተገጠመው የብርሀን መጠን መለኪያ ዝቅተኛ ብርሀን በሚኖሩባቸው ሁኔታዎች የአጭር እይታ መብራቱን በፍጥነት ያበራዋል፡፡


የላቁ የአኗኗርና የማሽከርከር ሁኔታዎች

ዘና ለማለት አዲስ ዘዴ
ሙሉ በሙሉ በድጋሚ በተዘጋጁት የውስጥ ዲዛይኖች
በምቾት ይኑሩ
በIVECO S-WAY ውስጥ በጀርባዎ ዘና/ደገፍ ብለው ይቀመጡና በቤትዎ ውስጥ ያሉ ያክል ይሰማዎ፡፡ ሙሉ በሙሉ በድጋሚ በተዘጋጁት የውስጥ ዲዛይኖች ምክንያት ከኋለኛው ክፍልም ሆነ ጋቢና ውስጥ ተቀምጠው በእያንዳንዱ የጉዞ ቅጽበት ይዝናኑ፡፡

የላቀ የማሽከርከር ምቾት
ሙሉ ሹፌሩ የሚቀመጥበት አካባቢ የተዘጋጀው ተጨማሪ ቦታና በጣም ጥሩ እይታ እንዲሰጥ ተደርጎ ነው፡፡
እያንዳንዱ ዝርዝር በጉዞ ላይ በሹፌሩ የሚጠበቁ ሁኔታዎችን በሚያሟላበት መልኩ በጥንቃቄ ተጠንቷል፡፡

እያንዳንዱን ነገር በቦታው ላይ ያገኙታል
ሰፊ ተደርጎ የተዘጋጀው አዲሱ ጋቢና በጥሩ ሁኔታ በተሰደሩ ከፍተኛ የመያዝ አቅም ባላቸው ክፍል ክፍሎቹ ምክንያት ሁሉንም እቃዎችዎን እንዲያስቀምጡ ያስችልዎታል፡፡
በቅርጽ የተሰራው የላይኛው መደርደሪያ እስከ 250 ሊትሮች ድረስ ከፍተኛ የመያዝ አቅም አለው፡፡

ይረፉ፣ ዘና ይበሉ እንዲሁም ጥሩ እንቅልፍ ይተኙ
በተመጣጠነ አቀማመጥ የተሰራው የምሽትማረፊያ ቦታ ዲዛይኑ የተዘጋጀው እርስዎን በምሽት ጥሩ እረፍት ከከፍተኛ ምቾት ጋር እንዲያገኙ ለማስቻል ታስቦ ነው፡፡
ባለ አንድ ደረጃ የሆነው የስረኛው አልጋ ለስላሳ ወይም ጠንካራ ፍራሾች የሚያገኙበት አማራጭ ይሰጥዎታል፡፡

በከፍተኛ ደረጃ ውጤታማ ሞተሮች

በበቂ ሁኔታ አቅም ያለው
IVECO S-WAY - High efficiency performance

በከፍተኛ ደረጃ ውጤታማ ሞተሮች
IVECO S-WAY ለሁሉም ትግበራዎች ተስማሚ የሆኑ የዩሮ III/V በቤንዚን እና በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ሞተሮች ሰፊ ምርጫ ይሰጣል፡፡ 2 መቀየሪያዎች እንዲሁም በዩሮ V ከ360 እስከ 570 የሚለያዩ እና በዩሮ Euro III 560 የሀይል መለኪያዎች ያሏቸው በቤንዚን የሚሰሩት ሞተሮች የሚድብ መሪ ሀይል/ጉልበት ይሰጣሉ፡፡

በከፍተኛ ደረጃ ውጤታማ ትራንስሚሽን
የኤሌክትሮኒክስ ፍሪሲዮን ያለው ባለ 12-ፍጥነት የHI-TRONIX አውቶማቲክ ትራንስሚሽኑ የምድቡን እጅግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በአይነቱ ተመራጭ የሀይል ቀያሪ ለክብደት ሬሺዮ እና ረጅም የትራንስሚሽን ዘይት መቀየሪያ ጊዜዎች ይሰጣል፡፡

ነዳጅ ቆጣቢ መሳሪያዎች
ያለ ስራ መባከንን መከላከያ/ Anti-idling መሳሪያው ሞተሩን ወዲያውኑ ይዘጋል፡፡ የስማርት ሞተር ተጓዳኞች/ Smart Engine Auxiliaries መስራታቸው አስፈላጊ በማይሆንበት ወቅት የሚፈጠር የሀይል ብክነትን ይከላከላሉ፡ የአየር ፍሪሲዮን ማመቂያ ለዋጭ ተቀያያሪ ማስነሻ ፓምፕ/Air Clutch Compressor Smart Alternator Variable Steering Pump.


በበቂ ሁኔታ ጉልበት/አቅም ያለው
በቤንዚን የሚሰራ ሞተር አቀማመጥ

ENGINE CURSOR 9
Common Rail
CURSOR 13
Common Rail

CYLINDRÉE
(Litres)
8.7
12.9
PUISSANCE
ch à tr/min
330 à 1 655 – 2 200
510 à 1 560 – 1 900570 à 1 605 – 1 900
COUPLE
Nm à tr/min
1 400 à 1 100 – 1 6552 300 à 900 – 1 5602 500 à 1 000 – 1 605
SYSTÉME DE
POST-TRAITEMENT
HI-SCRHI-SCR
የጋቢና አቀማመጥ

የቀኝ ጋቢናው ለሁሉም ተልዕኮ ያገለግላል
​​​​​​​​​IVECO S-WAY - Lineup

የቀኝ ጋቢናው ለሁሉም ተልዕኮ​ ያገለግላል

IVECO S-WAY ዲዛይኑ የተዘጋጀው ለአሽከርካሪው ከፍተኛ/ጠንካራ ትኩረት በመስጠት ሲሆን የአዲሱ ጋቢናው ዲዛይን ከፍተኛ ደረጃ ተላላፊ ደህንነትን ለማረጋገጥ በድጋሚና ተጠናክሮ ተዘጋጅቷል፡፡

አዲሱ ዲዛይን በተጨማሪም ለአሽከርካሪው በባለ አንድ ክፍል የጎን መስኮቶቹና የኋላ መመልከቻ መስታወቶቹ አማካኝነት በከፍተኛ ደረጃ የተሻሻለ ቀጥተኛ እይታ ይሰጣል፡፡


ሹፌሩን ማዕከል አድርጎ የተዘጋጀ ዲዛይን
የAS ርብራብ ጋቢና

ከወለል እስከ ጣሪያ ቁመት (ሴሜ)
ረጅም ጣሪያ: 215
አጭር ጣሪያ: 170
1 ወይም 2 ወለሎች


የAT ርብራብ ጋቢና

ከወለል እስከ ጣሪያ ቁመት (ሴሜ)
መካከለኛ ጣሪያ: 185
አጭር ጣሪያ: 125
1 ወይም 2 ወለሎች


አጭር ጣሪያ ያለው የAD አጭር ጋቢና

ከወለል እስከ ጣሪያ ቁመት (ሴሜ)
አጭር ጣሪያ: 125


የፎቶግራፍ ማዕከል

S-WAY: ከቤትዎ ወደ ሌላኛው ቤትዎ