Press release

አይቬኮ በኢትዮ ጵያ 160 ትራከር የጭነት መኪናዎችን ለ ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኃ.የተ.የግ ማህበር ያቀርባል

የአይቬኮ ትራከር የጭነት መኪናዎች ለኢትዮጵያና ለምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ጥራት ያለውን የምግብ ዘይት ለሚያመርተውና ለሚያከፋፍለው የፊቤላ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኮምፕሌክሰ ተልዕኮ በእጅጉ የሚመቹ ናቸው። 160ዎቹ ትራከር የጭነት ተሸከርካሪዎች ዝቅተኛ የእንቅስቃሴ ወጪ እና ከፍ ያለ የእንቅስቃሴ ደህንነትን ለአንቀሳቃሹ እንዲሁም ላቅ ያለ ምቾትን ለሾፌሩ በሚያቀርበው የዩሮቶኒክ ራስ ሰር የማርሽ ሳጥን የደረጁ ናቸው።

ቡሬ ከተማ፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን፣ አማራ ብሄራዊ ክልል፣ ኢትዮጵያ፣ ፌብሩዋሪ 7 2021።

አይቬኮ 160 ሞዴል AT380T38H 6x4 ጠንካራ ትራከሮችን እንዲሁም AT720T42TH 6x4 ትራክተር የጭነት መኪኖችን ለምግብ ዘይት (1.6 ሚሊዮን ሊትር በቀን)፣ ለዘይት ፍሬ ማድቀቂያ እንዲሁም ለያት ላሉ ቅባቶችና ለኦሊዮ ኬሚካሎች በመሪነት በኢትዮጵያ ለተቋቋመው ለፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኃ.የተ.የግ ማህበር አቅርቧል። ተሸከርካሪዎቹ ሊዘለቁ የማይችሉ ጎርባጣ መልከዓ ምድሮች ላይ ለመስራት ባላቸው አቅም እንዲሁም ከበድ ባሉ ሁኔታዎች የሚፈጠሩ ግፊቶችን እጅግ አስደናቂ ከሆነ አፈጻጸም ጋር በመወጣት የድርጅቱን ውስን ቴክኒካዊና ሙያዊ ፍላጎቶች ያሟላሉ። ትራከር የጭነት መኪናዎች ከጅቡቲ እስከ ቡሬ ያለውን መንገድ ለመሸፈን በጥቅም ላይ ይውላሉ።

ኢተትዮጵያ በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ከናይጄሪያ ቀጥሎ 110 ሚሊዮን ህዝብ በመያዝ ሁለተኛ ናት።  ገሪቱ ወደ 600 ሚሊዮን የዩኤስ ዶላር በአመት የምግብ ዘይት ከውጪ ለመግዛት ታወጣለች፤ ይህም የ ገሪቱን 25 ከመቶ የውጪ ምንዛሬ ወጪ ይሸፍናል። ከተፈለገው የምግብ ዘይት መጠን 95% እንደ ማሌዢያ፣ ኢንዶኔዢያ እና ሲንጋፖር ካሉ አምራች ሃገራት ታስገባለች። የኢትዮጵያ ገበያ የማብሰያ ዘይት ፍላጎት 507,191 ቶን በዓመት ነው፤ ከዚህም 95% ከውጪ የገባ የምግብ ዘይት ነው። አብዛኛው ጥቅም ላይ የሚውለው ዘይት የዘንባባ ዘይት ሲሆን በአካባቢ የሚመረተው የኒ ር የዘር ዘይት በሁለተኝነት ይከተለዋል። ስለዚህ የፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኃ.የተ.የግ ማህበር ተቋም ለ ገሪቱ የውጪ ምንዛሬ ከፍተኛ ቁጠባ በከፍተኛ ደረጃ አሰተዋጽኦ ያደርጋል።

ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኃ.የተ.የግ ማህበር በቡሬ ኢንዱስትሪዊ ከተማ ከአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሊዝ የተሰጠው መሬት 29 ሄክታር ይሸፍናል፤ በተጨማሪም ከአውሮፓ ሙሉ በሙሉ በተከፋፈለ መልኩ በመርከብ ለሚመጡ የአይቬኮ የከባድ ተሸከርካሪዎች መገጣጠሚያ የሆነው የበላይነህ ክንዴ ኢምፖርት አክስፖርት ቡድን አባል ነው።

አቶ በላይነህ ክንዴ፣ የበላይነህ ክንዴ ኢምፖርት አክስፖርት ዋና ስራ አስኪያጅ እንዳሉት ‘’ጥራት ያለው የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እንዲሁም በአካባቢው ከፍተኛ ጥራትና ከፍተኛ ተፈላጊነት ስላለን የተለየ ነገር በማቅረብ ገበያውን በቅርቡ ሰብሮ ለመግባት ተስፋ እናደርጋለን። የሚመጡ ጥሬ እቃዎች እንዲሁም የሚወጡ ያለቁ ምርቶች ስንቅና ትጥቅ በ ገሪቱ ባለፉት አስርት አመታት በነበራቸው በጉልበታቸው፣ አስተማማኝነታቸው፣ የአሰራር ብቃታቸውና ከፍተኛ የአገልግሎት መደባቸው አማካኝነት በመረጥናቸው በአይቬኮ ትራከር የጭነት መኪናዎች አማካኝነት ይከናወናል።’’

አንቶኒዮ ካሩሶ፣ የአምቼ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅበርክክቡ ወቅት ተገኝተው እንደተናገሩት ‘’እንደ ኤይቬኮ ተወካይ በመሆን የዚህ ከፍተኛ ጥቅም ያለው ፕሮ ክት ተካፋይ በመሆኔ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል። የሞተር ቴክኖሎጂ፣ የተለያዩ ክፍሎችና መገጣጠሚያዎች ስብጥር የአይቬኮ ትራከርን ሊቆም የማይችልና ጠንካራ ተግዳሮቶች ጋር የሚመጣጠን አቅም ያለው ያደርገዋል። የፊቤላ ፕሮ ክት የምግብ ዜትን ለኢትዮጵያ ዳርድንበሮች በማከፋፈል ልንጋፈጠውና ልናሸንፈው የምንፈልገው ትልቅ ተግዳሮት ነው።’’

ፋቢዮ ዴ ሴራፊኒ፣ የአይቬኮ አፍሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ዳይሬክተር ጨምረው እንዳሉት ‘’ከበላይነህ ክንዴ ኢምፖርት አክስፖርት ጋር በኢትዮጵያ ያለን ጠንካራ ትብብር የደንበኞቻችንን የቢዝነስ ፍላጎት ስናሟላ ጥራትና የላቀ አገልግሎት ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች የመሆናቸው ጽንሰ  ሳብ ላይ ትኩረት እያደረግን ምርጥ የትራንስፖርት መፍትሄ ለማቅረብ ያለንን ታማኝነትና ትጋት የሚያመለክት ማስረጃ ነው።’’