Press release

ኢቬኮ እና አምቼ ለአዳዲስ የጭነት ተሽከርካሪዎች አቅርቦት ከፔፕሲኮ ፉድስ ኢትዮጵያ (ሙሉ በሙሉ በፔፕሲኮ ባለቤትነት ከተያዘው ሰንሰለት ፉድ ፕሮሰሲንግ) ጋር በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡


በዚህም መሰረት ኢቬኮ እና አምቼ ዴይሊ እና ቲ-ዌይ የተሰኙ የጭነት ተሽከርካረ ሞዴሎቸችን ለፔፕሲኮ ፉድስ ኢትዮጵያ የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡ አዳዲሶቹ ተሽከርካሪዎች የፔፕሲኮ ፉድስ ኢትዮጵያን የእድገት ስትራቴጂ ለመደገፍ ቁልፍ ሚና የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ መጋቢት 04/2016 ..

ኢቬኮ በኢትዮጵያ የንግድ ስራ አጋሩ ከሆነው አምቼ ጋር በጋራ በመሆን ዴይሊ ቀላል እንዲሁም ኢቬኮ ቲ-ዌይ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ለረዥም ጊዜ ደንበኛው ፔፕሲኮ ፉድስ ኢትዮጵያ ያቀረበ ሲሆን ይህ አቅርቦትም ኩባንያው በተለይ በሀገሪቱ እጅግ ገጠራማ ቦታዎች የምርት ስርጭት ተደራሽነቱን እንዲያጠናክር የሚያግዘው ይሆናል፡፡

ዴይሊ ሞዴል ተሽከርካሪዎቹ በአዲስ አበባ በተከናወነው ስነ ስርዓት ርክክብ የተደረባቸው ሲሆን እነዚህ ተሽከርካሪዎች ባለ70C15/E3 4x2 ሻንሲና ጋቢና ተሽከርካሪዎች ናቸው፡፡ ተሸከርካሪዎቹ የተገጣጠሙት በአዲስ አበባ በሚገኛው የአምቼ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ሲሆን ፔፕሲኮ ፉድስ ኢትዮጵያ ምርቱን የሚያቀርብባቸውን ነባሮቹን የጭነት ተሽከርካሪዎች እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል፡፤

በተጨማሪም ኢቬኮ T-Way AT380T43H የጭነት ተሽከርካሪዎችን ያቀረበ ሲሆን እነዚህ ተሽከርካሪዎች የድንች ምርትን ከማሳ ወደ ፋብሪካው እንዲሁም በፋብሪካው የተመረቱ ምርቶችን ገጠራማ ወደሆኑ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለማሰራጨት የሚያገለግሉ ይሆናል፡፡

በተሽከርካሪዎቹ ርክክብ ላይ የተገኙት የአምቼ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አንቶኒዮ ካሩሶ በኢትዮጵያ በቀዳሚነት ትልቁ የድንች ቺፕስ አምራች ከሆነው ፔፕሲኮ ጋር በጋራ የምንሰራ በመሆናችን ደስተኞች ነን፡፡ አዲሱ ኢቬኮ ዴይሊ ሞዴል ተሽከርካሪ ለኢትዮጵያ ገበያ ካስተዋወቅን ወዲህ ባለፉት አራት አመታት ከድርጅቱ ጋር እየሰራን የምንገኝ ሲሆን ከዚ ጊዜ ወዲህም ኩባንያው የብራንዳችን ታማኝ ደንበኛ ሆኖ ዘልቋል፡፡ ከዚህም በላይ በአዲስ አበባ በርካታ ደንበኞች ዴይሊ ቫኖችን የፔፕሲኮ ፉድስ ኢትዮጵያ መለያ ምርት የሆነው ሰን ቺፕስ ቫን ብለው እስከመጥራት ደርሰዋል፡፡ በዴይሊ አማካኝነት ምርጥ በሆነ የስራ አካባቢ የላቀ እጅግ ምቹ እና ጥራት ያለው የማሽከርከር ልምድን በማግኘታቸው ደስተኞች ነን፡፡

የፔፕሲኮ ፉድስ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑ ክሪስ በበኩላቸው ፔፕሲኮ ለስራው ወደ 46 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የመደበ ሲሆን ይህ ደግሞ ኩባንያው አገሪቷ ባላት የኢኮኖሚ እድገት ላይ ያለውን እምነት የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ኢንቨስትመትን ከፍተኛ የሆነ ተጨማሪ የስራ እድሎችን የፈጠረ ሲሆን በተጨማሪም ኩባንያው የምርት አቅሙን በአስር እጥፍ እንዲያሳድግ የሚያግዘው ይሆናል፡፡ የቀረቡልን ተሽከርካሪዎች የድንች ሰብል ምርትን ከማሳ መስኮች ወደ ፋብሪካው ለማጓጓዝ እና የፋብሪካ ምርቶችን በመላው ኢትዮጵያ ገጠራማ ቦታዎች ለማዳረስ የሚያስችሉ በመሆናቸው ሰን ቺፕስ በሀገሪቱ አሁን ካሉት ታማኝ ደንበኞች በተጨማሪ ሌሎች ደንበኞችን ለማፍራት የሚያስችለው ይሆናል፡፡ ፔፕሲኮ ፖዘቲቭ (ፔፕ+) የመጨረሻ ተጠቃሚ ላይ ትኩረት ያደረገ የዘላቂነት ስትራቴጂያችን ሲሆን ይህም ስትራቴጂ በኢትዮጵያ የተሻለ ዘላቂ የሆነ የምግብ ስርዓት ግንባታ ላይ አስተዋጽዖ በማድረግ የፕላኔታችን ተፈጥሮአዊ ሀብቶች በሚጠብቅ መልኩ የአለም አቀፍ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ልማትን በማገዝ የሰው ልጅ ፍላጎቶችን የማሟላት ግብ ያለው ስትራቴጂ ነውበማለት ገልጸዋል፡፡

ኢቬኮ ዴይሊ ፡ ለምኞትዎ ጉልበትን ያጎናጽፉ

ዴይሊ በሚመደብበት የተሽከርከሪ መደብ ውስጥ እጅግ ሁለገብ ተሽከርካሪ ሆኖ የሚወሰድ ተሽከርካሪ ነው፡፡ በጥንቃቄ የተዘጋጀው ሞዴሉ እና የተሽከርካሪ አካል (ቦዲ) ስራ አማራጮቹ ለበርካታ አገልግሎቶች ለመዋል አመቺ ያደርገዋል፡፡ ተልዕኮዎ ምንም ይሁን ምን ዴይሊን ልክ እርሶ ላሰቡት የስራ እንቅስቃሴ እና ንግድ በሚያመች መልኩ ማግኘት እና ማስተካከል ይችላሉ፡፡

ዴይሊ ተሽከርካሪ በኢንዱስትሪው ዘርፈ ብዙ አማራጭ ያለው ሲሆን ተሽከርካሪው ከሚመደብበት ከ3.5 ቶን እስከ 7.2 ቶን ጠቅላላ ክብደት መደብ ውስጥ ካሉ ሌሎች ተሽከርካሪዎች በተለየ መልኩ ከ3000 እስከ 5100 የሚሆን ዊልቤዝ (ከፊት እግር እሰከ ኋላ እግር ያለው ርቀት) ያለው መሆኑ ከከተማ የምርት አቅርቦት እስከ ግንባታ ዘርፍ ከባድ የትራንስፖርት ስራዎን ለማከናወን አማራጮች ያሉት ተሽከርካሪ ነው፡፡ ተሽከርካሪው ገደብ የለሽ የቦዲ ወርክ አማራጮች ያሉት በመሆኑ ለፈለጉት አላማ በሚገባ መቀያየር/ማስተካከል ማድረግ ያስችልዎታል፡፡ እጅግ ልዩ ሁኔታ እንቅስቃሴ እና ጥንቃቄ ለሚፈልጉ እንደ ህይወት አድን ተሽከርካሪ ወይም አምቡላንስ ተግባራት አቻ የማይገኝለት ነው፡፡

አዳዲሶቹ ሚሞሪ ፎም ወንበሮች፡ ለሾፌር እጅግ ከፍተኛ ምቾትን የሚያጎነጽፉ ናቸው፡

ዴይሊ በቀላል የንግድ ተሽከርካሪዎቸ የመጀመሪያው የሆነው ሙሉ በሙሉ በሚሞሪ ፎም የተሰራ ማዕከላዊ የወንበር ስፖንጅ (ፓድ) እና የጀርባ መደገፊያ መቀመጫ ያለው ተሽከርካሪ ነው፡፡ ሞልዱ አካልን አቅፎ የሚይዝ፤ የሰውነት ክብደትን አመጣጥኖ የሚያሳርፍ ግፊትን እስከ 30% መቀነስ የሚችል ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከፍተኛ ምቾት የሚሰጥ እንዲሁም የጀርባ ህመምን የሚከላከል ያደርገዋል፡፡ የጎን እና ጎን ክፍሎቹም ባለ 15 ሚሜ ከፍተኛ ጥብቀት (ዴንሲቲ) ባለው ፎም የተሰራ በመሆኑ የሾፌሩ አካል በሚገባ ቦታውን እንዲይዝ የሚያስችል ሲሆን ይህ ደግሞ ደህንነትን በመጨመር መልካም የሆነ የማሽከርከር ሂደት/ልምድ እንዲኖር ያስችላል፡፡ ቁመታቸው ረዘም ያለ ሰዎች የጋቢና መቀመጫው በ20 ሚሜ በሚረዝም እና 15 ሚሜ የበለጠ ውፍረት ባለው መቀመጫ ትራስ አማካኝነት ረዘም ላሉት እግሮቻቸው የተሻለ ድጋፍ ይኖራቸዋል፡፤ የመቀመጫው የጎን ማንቀሳቀሻ እጀታዎች ወደ ተሽከርካሪው ለመግባት እና ከተሽከርካሪ ለመውረድ እጅግ ቀላል የሚያድርጉ በመሆናቸው በተደጋጋሚ ከተሽከርካሪው መውረድ ለሚያስፈልጋቸው ተግባራት እና የበር ለበር ምርት አቅርቦት እጅግ አመቺ ነው፡፡

ኢቬኮ ቲ-ዌይ፡ ይህ እጅግ አስቸጋሪ ለሆኑ ቦታዎች እጅግ አስተማማኝ እና ከፍተኛ የስራ ውጤት ያለው ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ነው፡፡

ኢቬኮ ቲ-ዌይ ብራንዱ የሚታወቅበትን የጠጠር መንገድ የረዥም ርቀት የመጓዝ ችሎታ/ጥንካሬ እና አስተማማኝነትን ጠብቆ የተሰራ ተሽከርካሪ ነው፡፡ ይህ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ በምርታማነት፣ በጭነት አቅም፣ በደህንነት እና በሾፌር ምቾት ረገድ ከሚጠበቀው በላይ እጅግ ዘመናዊነትን ይዞ የመጣ ተሽከርካሪ ነው፡፡፡

ለጥንካሬ፡ ተሽከርካሪው ዲዛይን የተደረገው ጥንካሬ እና አስተማማኝነት እንዲኖረው ተደርጎ ነው፡፡

የኢቬኮ ቲ-ዌይ ተሽከርካሪ በማናቸውም የፒስታ ምንገዶች ላይ ምርጥ በሚባል ደረጃ በጥንካሬ እና ቶርሽናል ሪጂዲቲ ረገድ ቁጥር አንድ ሆኖ ዲዛይን የተደረገ ተሽከርካሪ ነው፡፡ የቀደሙት ሞዴሎች የነበራቸውን ከፍተኛ ጥንካሬ ያለው ባለ 10 ሚሜ ውፍረት ፍሬም ሻንሲን በ177 ኪሎ ኒውተን ሚትር ጭነት ላይ መተጣጠፍ ከሚችለው የሻንሲው የላይኛው ክፍል ጋር አጣምሮ የያዘ ነው፡፡ የፊት ለፊት አክስሉ እስከ 9 ቶን ጭነት መሸከም የሚችል ነው፡፡

በፊት ለፊት አክስሉ ላይ የሚገኘው ሀብ ሪዳክሽን የበለጠ ጥንካሬ እና አገልግሎት እንዲኖር አንድ መስፈርት ነው፡፡ ​

አዲሱ ከፍተኛ አቅም/ጥንካሬ ያለው የፊት ለፊት የታንደም አክስሎች ሰስፔንሽን ሲስተም የተሽከርካሪውን ክብደት በማመጣጠን በፒስታ መንገድ ላይ ከፍ ብሎ እንዲጓዝና ጉዞ በሚጀምርበትም ጊዜ የተሻለ መነሻ አንግል እንዲኖረው የሚያስችል ነው፡፡

የኢቬኮ ቲ-ዌይ ከባድ ተሽከርካሪ እስከ 470 የፈረስ ጉልበት እየጨመረ በሚሄድ የኢቬኮ አስተማማኝ እና ውጤታማ ከርሰር 13 ሞተር (ባለ13 ሊትር) አማካኝነት መሬት ለመቆንጠጥ እና ለPTO የሚያስፈልገውን ጉልበት በሚገባ መስጠት የሚችል ተሽከርካሪ ነው፡፡

ሞተሩ በተግባር አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ ሀይ-ትሮኒክስ አውቶሜትድ ጊር ቦክስ (ካምቢዮ) የተገጠመለት ሲሆን ይህ ክፍል የዳገት ላይ መንሸረታት ማገጃ (ሂል ሆልደር)፣ በአንሸራታች ሁኔታዎች ውስጥ ትራክሽንን ለመመለስ እና ተሽከርካሪው በማይጓዝበት ወቅት ሞተሩ እጅግ በዝግታ እንዲዞር የሚያደርግ ክሪፕ ሞድ፣ በጉዞ ወቅት ደግሞ የተሽከርካሪውን የእንቅስቃሴ ጉልበት (ኢነርሺያ) በመጠቀም በቁልቁለት ወቅት የማርሽ አቀያየርን የበለጠ አስተማማኝ የሚያደርገው ኢኮሮል ክፍል የመሳሰሉ በተለይ ለፒሰታ መንገድ ጉዞ ተብለው የተሰሩ ክፍሎች ያሉት ነው፡፡

ሀይ-ትሮኒክስ በአውቶሜትድ ትራንስሚሽን ዘርፍ እጅግ ዘመናዊ የሚባለው ስሪት ሲሆን በማናቸውም ሁኔታ ምርጥ የሆነ የማርሽ መቀየር ችሎታን የሚያገናጽፍ ነው፡፡

ስለ ፔፕሲኮ

የፔፕሲኮ ምርቶች በአለም ዙሪያ ከ200 በላይ በሆኑ አገራት ውስጥ በሚኖሩ ሸማቾች በቀን ከአንድ ቢሊዮን ጊዜ በላይ ፍጆታ ያላቸው ተመራጭ ምርቶች ናቸው፡፡ ፔፕሲኮ ሌይስ፣ ዶሪቶስ፣ ቺቶስ፣ ጋቶራዴ፣ ፔፕሲ ኮላ፣ ማውንቴይን ዱ፣ ኩዌከር እና ሶዳ ስትሪም የተሰኙ ብራንዶች ጨምሮ በሚያቀርባቸው ምርቶቹ በ2023 ... 91 ቢሊዮን ዶላር በላይ የተጣራ ትርፍ አግኝቷል፡፡ የፔፕሲኮ ምርት አይነቶች በርካታ በሸማቾች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑና ምግብ እና ለስላሳ መጠጦችን የሚያካትት ሲሆን ከእነዚህም መካከል በአለም ዙሪያ ዝነኛ የሆኑ እና እያንዳንዳቸው በአመት በግምት ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር የችርቻሮ ገቢ የሚያስገኙ የኩባንያው መለያ ምርቶች ይገኙበታል፡፡

ፔፕሲኮ የሚከተለው ራዕይ ከፔፕ+ ጋር በማሸነፍ በለስላሳ መጠጦች እና መክሰስ ምርቶች አለም አቀፍ ቁጥር አንድ መሪ መሆን ነው፡፡ ፔፕ+ እሴትን እና የፕላኔታችን የተፈጥሮ ሀብቶች በጠበቀ መልኩ ስራችንን ለማከናወን ዘላቂነትን እና የሰው ካፒታልን ማዕከላዊ ትኩረቱ ያደረገ ሁሉንም ያካተተ የለውጥ (ትራንስፎርሜሽን) የማምጣት እንዲሁም ለፕላኔታችን እና ሰዎች የመልካም ለውጥ አርአያ የመሆን ስትራቴጂ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ www.pepsico.com መጎብኘት እንዲሁም በX (Twitter), Instagram, Facebook, and LinkedIn @PepsiCo ሊከተሉን ይችላሉ፡፡