Press release

አይቬኮ እና አምቼ 15 ዴይሊ ተሸከርካሪዎች ለኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አክሲዮን ማህበር የኮካ-ኮላ ለስላሳ መጠጦች አምራች እና አከፋፋይ በኢትዮጵያ አስረከቡ


  • ለሁለገብነት ዝናው ታማኝ የሆነው አይቬኮ ቀላል የንግድ ተሽከርካሪ በከተማ ውስጥ ዕቃዎችን ከማከፋፈል እስከ ከባድ ጭነት ትራንስፖርት ድረስ መጠነ ሰፊ የተለያዩ ተልእኮዎችን ይፈጽማል፡፡

  • ከምቹ ስፖንጅ የተሰሩት የሹፌር መቀመጫ፣ የጀርባ እና የጭንቅላት መደገፊያ ለአሽከርካሪው ተጨማሪ ምቾትን ይሰጣሉ፡፡ 



አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 052016 .

አይቬኮ እና በኢትዮጵያ የንግድ ወኪሉ የሆነው አምቼ ለመጀመሪያ ጊዜ ለማንኛውም ተልእኮ ፍጹም ምቹ የሆኑ በቁጥር 15 ዴይሊ የቀላል ጭነት ተሽከርካሪዎችን ለረዥም ጊዜ ደንበኛቸው ለሆንው ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አክሲዮን ማህበር (EABSC) ብቸኛ የኮካ-ኮላ ምርቶች አምራች እና አከፋፋይ በኢትዮጵያ አስረከቡ፡፡ አምቼ እስከ አሁን ድረስ ላለፉት 16 ዓመታት ከኮካ ኮላ የለስላሳ መጠጦች አፍሪካ የንግድ አጋሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዓለም ታዋቂ ለሆነው ለዚህ የለስላሳ መጠጦች አምራች ኩባንያ በየዓመቱ አይቬኮ የከባድ ፤የመካከለኛና ቀላል ጭነት ተሽከርካሪዎችን ሲሸጥ የነበረና በጥቅሉ በቁጥር ከ200 በላይ የአይቬኮ የጭነት ተሸከርካሪዎችን አቅርበዋል፡፡

በአምቼ በታህሳስ 05 ቀን በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ የተረከቡት ሁሉም የአይቬኮ ምርት የሆኑት Daily70C15/E3፣ ባለ ሁለት አክስል ተሽከርካሪዎች ናቸው፡፡ እነዚህ በአምቼ መኪና መገጣጠምያ የተገጠሙት ተሽከርካሪዎች ኮካ-ኮላ ኩባንያ ምርት ማከፋፈል ስራ ላይ ከተሰማሩት ሌሎች ተሸከርካሪዎች ጋር አብሮ ይሰማራሉ፡፡

በተሽከርካሪዎቹ ርክክብ ላይ የተገኙት የአምቼ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አንቶኒዮ ካሩሶ፡ በዚህ ስኬት እጅግ ተደስቻለሁ፡፡ ይህ ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አክሲዮን ማህበር ጋር የተደረገው ርክክብ አይቬኮ በኢትዮጵያ ውስጥ በደንበኞቻችን ዘንድ የመጀመሪያ ምርጫ መሆኑን የሚያሳይ ከመሆኑም ባለፈ በተስማሚ የስራ ሁኔታ የአይቬኮ ዴይሊ የላቀ የማሽርከር ተሞክሯችንን ስናቀርብ ደስ እያለን ነው፡፡በማለት ተናግረዋል፡፡

የአምቼ የሽያጭ ክፍል ተወካይ የሆኑት አቶ መኮንን ተስፋዬ: “ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ አክሲዮን ማህበር ጋር የተካሄደው የንግድ ስምምነት አካል በመሆኔ ደስተኛ ከመሆኔም ባለፈ በሂደቱ ወቅት በሁለቱም ኩባንያዎች የስራ ሀላፊዎች ለተደረገልኝ ድጋፍ በእጅጉ አመሰግናለሁ፡፡’’ በማለት አክለዋል፡፡

አይቬኮ ዴይሊ:የህልምዎን መኪና ያሽከርክሩ
ዴይሊ በአይነቱ ሁለ ገብ ተሽከርካሪ ነው፡፡ የተሽከርካሪው የላቀ አገጣጠምና የአካል ስራ አማራጮቹ መጠነ ሰፊ እድሎችን የሚፈጥሩ

ሲሆን ተልእኮዎ ምንም ይሁን ምን ዴይሊን ለንግድ ስራዎት መስፈርቶችዎ ፍጹም ተስማሚ ሆኖ ያገኙታል፡፡

ዴይሊ ለገበያው የተለያዩ አማራጮች ያቀርባል - ተሽከርካሪው ከ3.5 እስከ 7.2 ቶን ጠቅላላ ክብደት የሚጭን፣ ከ3000 እስከ 5100 ሚሜ የጎማ ርቀት ያለው ተሽከርካሪ በማቅረብ በአይነቱ የመጀመሪያ ሲሆን ይህም በከተማ ውስጥ ዕቃዎችን ከማከፋፈል እስከ ግንባታው

ዘርፍ የከባድ ጭነት ትራንስፖርት ስራዎች ድረስ ለተለያዩ አይነት ተልእኮዎች መጠነ ሰፊ እድሎችን ይከፍታል፡፡ ተሽከርካሪው የተዘጋጀው በተለያዩ አይነት የአካል ስራ አማራጮች መሆኑ ለልዩ ልዩ ፍላጎቶዎችን ለሟማላት ቀላል ያደርገዋል፡፡ ተሽከርካሪው እንደ የህይወት አድን ተሽከርካሪ ወይም አምቡላንስ ላሉ ልዩ ሙያዎች ፍጹም ተስማሚ ነው፡፡

አዲስ ምቹ የስፖንጅ ወንበሮች: ለሹፌሩ ከፍተኛ ምቾት እንዲሰጡ ታስበው የተዘጋጁ

ከስፖንጅ የተሰሩ የመቀመቻና የጀርባ መደገፊያ ክፍል ያለው ሙሉ በሙሉ አዲስ የሹፌር ወንበርን የሚይዙት የዴይሊ ስሪቶች - የኢንዱስትሪው የመጀመሪያ ቀላል የንግድ ተሽከርካሪዎች ናቸው፡፡ የሰውነት ክብደትን በምቾት እንዲያሳርፍ ተስተካክሎ የተሰራው የስፖንጅ ወንበር የሰውነት ክብደት ጫናን በ30% ይቀንሳል፡፡ ይህም እጅግ ከፍተኛ ምቾት ከመስጠቱም ባለፈ የጀርባ ህመምን ይከላከላል፡፡ የጎን መደገፊያዎቹ ዘና ብሎ መደገፍን፣ ደህንነትን እና የማሽከርከር ተሞክሮን ለማሻሻል 15 ሚሜ ውፍረት ካለው ስፖንጅ የተሰሩ ናቸው፡፡ ለረጃጅም ሰዎች 20 ሚሜ ርዝመትና 15 ሚሜ ውፍረት ያላቸው ባለመደገፊያ የፊት ወንበሮች የተዘጋጁለት መሆኑ እግሮቻቸውን በአግባቡ እንዲያስደግፉ ያስችሏቸዋል፡፡ የጎን መደገፊያዎቹ በቀላሉ ወደ ተሽከርካሪው ለመግባት እና ለመውረድ እንዲያስችሉ ተደርገው መዘጋጀታቸው ተደጋጋሚ መውጣትና መውረድን ለሚጠይቁ የቤት ለቤት የማከፋፈል ስራዎች አቅርቦቶች ተመራጭ ያደርገዋል፡፡