ጥንካሬው

አዲሱ ዴይሊ (DAILY) ከቀላል የንግድ ተሽከርካሪዎች ጠንካራ እና በጣም ዘላቂ አፈፃፀም አለው።

ጥንካሬው በቻንሲው ላይ የተመሠረተ፣ በ C-ሴክሽን የጎን ደጋፊዎች ልዩ ብረት የተሰራ መሆኑ ፣ ዴሊን እየተነዱ ከምናገኛቸው ቀላል የንግድ ተሽከርካሪዎች ውስጥ የተለየ የሚያደርገው ልዩ ገጽታው ነው።

ዴይሊ ጠቀላላ ክብደቱ እስከ 7 ቶን ሲሆን የሚሸከመው የጭነት መጠን 4700 ኪ.ግ የሚደርስ ብቸኛ ቀላል የንግድ መኪና ነው። የፊት እና የኋላ አክስ የመጫን አቅሙ ከፍተኛ ሲሆን ካሉት ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠው ነው ፡፡

ጋቢናውን እና ርዝመቱን ሳይቀይር ከ 3000 እስከ 4750 ሚ.ሜ ዊልቤዝ ማግኘት ይቻላል፡፡ ይህ በቀደሙት ሬንጆች ውስጥ ቻንሲ ላይ ያሉት ዕቃዎች በአዲሱ DAILY ላይም መጠቀም ያስችላል።

የአዲሱ ዴይሊ ቻንሲ ካብ በጣም የተለመደ የተሽከርካሪ አካል አምራቾችም አንፃር ጠንካራ እና ለመስራት ቀላሉ ነው ፡፡ ባለ አንድ ጋቢና ፣ የተሳፈሪ መጫኛ እና ቻሲ ካውል ሰሪት ውስጥ ነጠላ ወይም መንታ ጎማዎች ፣ እንደ ሳጥን ቫን ሆኖም ያገለግላል ፣ ገልባጭ መኪና ፣ የፓነል ቫን ፣ ካምፕ መኪና ፣ ሚኒባስ ፣ የተሽከርካሪ የጥገና መኪና ፣ የክሬን መኪና ፣ ፍላት መኪና እና ለብዙ ሌሎች አገልግሎቶች መጠቀም ይቻላል።

ጠንካራ ነው ማለት ማንኛውንም ሥራ መሥራት ይችላል ማለት ነው ፡፡

የቫኑ አቅም የተመቻቸ እንዲሆን ተደርጋል ፣ በጠቅላላው ርዝመት እና በጭነት ክፍል ርዝመት ላይ አዲሱ የ 3520 እና የ 4100 ሚ.ሜ ዊልቤዝ ተሽከርካሪ በመሬት ልኬቶች እና በመጫኛ መድረክ ላይ ምንም ተጽዕኖ ሳያስከትሉ የኋላ መከለያውን ይቀንሳሉ። በዚህ መንገድ ከ 9 እስከ 20 ሜ3 ባለው ውስጥ ሙሉ በሙሉ አዲስ የመጫኛ አቅም ተጥራል፡፡
አዲሱ 18 እና 19.6 ሜ3 ሞዴሎች የተመረጡ ናቸው ለማንኛውም የጭነት (ቮልዩም) መጠን ስለሚገኙ፡፡